Telegram Group & Telegram Channel
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 11 | #_ቅዱስ_ያሬድ ተሰወረ።

ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ።

ሊቁ በሕጻንነቱ ትምህርት አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር። ትምህርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም። በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ።

ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር። ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር። አንድ ቀን ግን መምህሩ የነገሩት ቀለም አልያዝህ አለው። ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ።

ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምህሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው።

ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምህሩ ተመልሶ ይቅርታ ጠይቆ ትምህርት ጀመረ። ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ።

ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት። ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት። ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት አደረሱት።

ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር፣ ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ። ይህንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት።

ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ። ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ።

በ576 ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል።

የቅዱሱ ጸሎትና በረከት ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን።       
#_እንኳን_አደረሳችሁ
            ▸ www.tg-me.com/jp/አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ/com.Ewnet1Nat

tg-me.com/Ewnet1Nat/13328
Create:
Last Update:

BY አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

Share with your friend now:
tg-me.com/Ewnet1Nat/13328

View MORE
Open in Telegram

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

A Telegram spokesman declined to comment on the bond issue or the amount of the debt the company has due. The spokesman said Telegram’s equipment and bandwidth costs are growing because it has consistently posted more than 40% year-to-year growth in users.

Mr. Durov launched Telegram in late 2013 with his brother, Nikolai, just months before he was pushed out of VK, the Russian social-media platform he founded. Mr. Durov pitched his new app—funded with the proceeds from the VK sale—less as a business than as a way for people to send messages while avoiding government surveillance and censorship.

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ from jp

Telegram አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
FROM USA